በድሮ ዘመን አንዲት ጥንቸልና አንድ ጅብ በአንድ ላይ ይኖሩ ነበር፡፡ ጥንቸል በጣም ጎበዝ ነበረች፡፡ ሁሌም ከሰነፉ ጅብ በተሻለ ብዙ ምግብ የምታከማቸው ጥንቸል ነበረች፡፡ ጅቡ ስራ ላይ በጣም ሰነፍ ቢሆንም ምግብ መብላት ግን በጣም ይወድ ነበር፡፡ ምን ይፈጠር ይሆን?